ቀጥተኛ ፀጉር መትከል (DHI) በጣም የረቀቀ የፀጉር አሠራር ዘዴ ሲሆን በዚህ ዘዴ የፀጉር አሠራር በጥቅል ይከናወናል። ይህ ይበልጥ ተፈጥሯዊ መልክ እንዲኖረው ቀላል ያደርጋል። ነቅለ-ተከላው የፀጉር ስሮች የማገገም ጊዚን ስለሚያሳጥር የፀጉር መርገፍን ይቀንሳል። የነቅለ-ተከላው ብዕር የአተካከል አንግል እና አቅጣጫን ቀላል ስለሚያደረግ የተተከሉ የፀጉር ፎሊክሎችን ማዕዘኖች በቀላሉ ለማስተካከል ይረዳል። ያለውን ፀጉር ሳይጎዳ በአካባቢው በቀጥታ ለመትከል እድል የሚሰጠው የዲኤችአይ ዘዴ፤ ፀጉራቸው ረግፎ ላላለቀ ታካሚዎች የተሻለ ጥቅም ይሰጣል። ፀጉር በሚተከልበት ጊዜ ልክ በፀጉሩ ስፋት ብቻ ቀዳዳዎች ሰለሚከፈቱ ቀዶ ጥገናው በትንሽ ጉዳት ይጠናቀቃል.
ይህ በንቅለ-ተከላ ስኬታማነት ላይ ተጽእኖ የሚያሳድር ሁለተኛው ምክንያት ሲሆን በዲአይአይ ዘዲ ያለምንም ጥበቃ ስራዎች ስለሚሰሩ ከፍተኛ ጠቀሜታዎች ተገኝተዋል። የፀጉር ፎሊክሎች ከተሰበሰቡ በኋላ መተከያ ቻናል በሚከፈትበት ጊዜ ተተካይ ጸጉሮች ለ 3-4 ሰአታት ይቀመጣሉ። ምንም እንኳን በልዩ ውህድ እና በልዩ ማቀዝቀዣዎች ውስጥ ቢቀመጡም ከተፈጥሯዊ ሁኔታቸው ውጭ በመጠባበቅ ላይ ያሉ የፀጉር ፎሊክሎች በየደቂቃው ትንሽ ቢሆንንለጉዳት ተጋላጭ ናቸው። የዲአይአይ ዘዴ ትልቁ ጥቅምም የፀጉር ፎሊክሎች ከተሰበሰቡ በኋላ ከ3-4 ሰአታት ሳይቀመጡ ወዲያውኑ ይተከላሉ። ይህም በመጠባበቅ ምክንያት የሚከሰተውን የፀጉር መርገፍ/መጎዳት ይከላከላል.
በዲኤችአይ ንቅለ-ተከላ ዘዴ ውስጥ የተሻሻለው ሌላው ነጥብ የፀጉሮዎች ንቅለ-ተከላ ማዕዘኖች ናቸው። በዲኤችአይ ዘዴ የቻናልን የመክፈት ሂደት ከፀጉር ንቅለ-ተከላ ጋር አብሮ ስለሚሰራ፤ ዶክተሩ የፀጉሩን አንግል እና ጥልቀት በቀላሉ ሊወስን ይችላል። ይህ ተፈጥሯዊ ፀጉር እንድናገኝ የሚያስችለንን ጊዜን ይቀንሳል.
የግንባር መስመር ሁልጊዜ ስለሚታይ በትክክል አስምሮ ማቀድ ጥሩ የፀጉር ንቅለ-ተከላ ውጤትን ለማስገኘትት ከሚጠቅሙ ወሳኝ ነገራቶች አንዱ ነው። በዚህ ዘዴ ዶክተሩ ጠባብ አንግሎችን (ሰፋ ብሎ ጥቅጥቅ ያለ ንቅለ-ተከ የሚያስፈልጋቸው) በመጠቀም የግንባር መስመርን ማስመር ቀላል ያደርገዋል። ወደ ግንባሩ አካባቢ ሲደርስ 20 ዲግሪ ሊሆኑ የሚችሉ የቻናል ማዕዘኖች “በፀጉር ተከላ ብዕር” በቀላሉ ሊተከሉ ይችላሉ።.
የዲኤችአይ ፀጉር ንቅለ-ተከላ ደረጃዎች በቅደም ተከተል እነዚህን ይመስላሉ ፦ ተተካይ ፀጉር ፎሊክሎችን መሰብሰብ, የተከላ ቻናሎችን መክፈት እና የፀጉር ፎሊክሎችን መትከል። የ DHI ብዕር መሰል መሳሪያን በመጠቀም ተፈላጊውን የፀጉር ስር ከወሰዱ በኋላ ዶክተሮቹ በሚተከልበት ቦታ ላይ በጥቂት ሰከንዶች ውስጥ ቻናል ከፍትው የፀጉሩን ስር በተመሳሳይ ጊዜ ያስቀምጣሉ። በሌሎች ዘዴዎች ይህ ሂደት በሁለት ደረጃዎች ሲከናውን ነገር ግን እንደ ብዕር የሚመስለውን ይህን የ DHI የሕክምና መሣሪያ በመጠቀም, ይህ ሂደት ወዲያውኑ ይከናወናል።
ለፀጉር ትራንስፕላንት በሁለቱ ጆሮዎች መካከል ያለው ቦታ ይመረጣል ምክንያቱም እዛ አካባቢ የፀጉር ሥር ጠንከር እና ጥቅጥቅ ያለ ነው። የፀጉር ንቅለ-ተከላ ከራስ ፀጉር ተወስዶ የሚሰራ ስለሆነ, የጆሮ አካባቢ ትንሽ ፀጉር ያለው እና ሰፊ መተከል የሚያስፈልግው ጸጉር የሊለው ቦታ ላለው ሰው የሚጠበቀው አርኪ ውጤት ሊሰጥ አይችልም። በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታዎች ከሊላ የጭንቅላት አካባቢ ለጋሽ ቦታዎች ጥቅም ላይ መዋል አለባቸው፤ ይህ ደግሞ በተፈጥሯዊ መልክ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ የሚያሳድር ሁኔታ ነው። በፀጉር ንቅለ-ተከላ ውስጥ በአብዛኛው ጥቅም ላይ የሚውለው ለጋሽ ቦታ የአንገት ማጅራት አካባቢ ነው። ከዚህ በተጨማሪ አንዳንድ ሌሎች አካባቢዎች በሀኪሙ ምክር ለጋሽ ቦታ ሊሆኑ ይችላሉ።
ከ50% በላይ የሚሆኑ ወንዶች 50 ዓመት እስኪሞላቸው ድረስ በተለያየ ደረጃ የፀጉር መርገፍ ያጋጥማቸዋል። በአንዳንድ ሰዎች የፀጉር መርገፍ ገና በ20 ዓመት ሊጀምር ይችላል። አብዛኛውን ግዚ በወንዶች ላይ የፀጉር መርገፍ ዋነኛው መንስኤ Androgenetic alopecia ነው። በሌላ በኩል ደግሞ, በአንዳንድ ሁኔታዎች, የፀጉር እድገት ዑደት ውስጥ በሚፈጥር ቀላል በሆነ ችግር የፀጉር መርገፍ ሊከሰት ይችላል። ዋና ዋና ሕመሞች፣ ቀዶ ጥገናዎች ወይም አሰቃቂ ሁኔታዎች የፀጉር መርገፍን ሊያስከትሉ ይችላሉ። የታይሮይድ በሽታ፣ የደም ማነስ፣ የፕሮቲን እጥረት፣ ሁለተኛ ደረጃ ቂጥኝ፣ ኬሞቴራፒ እና ዝቅተኛ የቫይታሚን መጠን የፀጉር መርገፍ ሊያስከትሉ ይችላሉ።
የሴቶች የፀጉር መርገፍን በተመለከተ ያሉት ምክንያቶች ከወንዶች የተለዩ ናቸው። በቂ የሆነ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እና እንደ አልኦፔሲያ ያሉ አንዳንድ በሽታዎች ወይም ከሆርሞኖች ጋር የተያያዙ አንዳንድ በሽታዎች የፀጉር መርገፍ ሊያስከትሉ ይችላሉ። በዚህም ምክንያት የፀጉር መርገፍ መንስኤዎችን ለማከም የፀጉር ቀዶ ጥገና ከመደረጉ በፊት አጠቃላይ የሕክምና ምርመራ ማድረግ አስፈላጊ ነው።
የዓመታት ልምድ
ጤና ጣቢያዎች
ዶክተሮች እና ሰራተኞች
አገልግሎት የሚሰጡ ሀገራት
Copyright © 2022 Sultan Hair. All Rights Reserved.