የ FUE ዘዴ ህመም የሌለበት እና ምንም አይነት ጠባሳ የማይተው ስለሆነ ቅንድብን ለመትከል በጣም ጥሩው ዘዴ ነው። የዚህ ዘዴ ትልቅ ጥቅሙ የንቅለ-ተከላው ውጤት በፍጥነት ይታያል.በአካባቢው የበለፀገ የደም ፍሰት ስለሚገኝ በአራተኛው ወር ውስጥ የቅንድብ ጸጉሮች ማደግ ይጀምራሉ። የቅንድብ ንቅለ-ተከላ ከተደረገ በኋላ እስከ አንድ አመት ድረስ የቅንድብ ፀጉር ማደጉን ይቀጥላል.
ለቅንድብ ንቅለ-ተከላ የሚውሉ የፀጉር ፎሊክሎች(ስሮች) ከጀርባ ጭንቅላት ላይ የሚሰበሰቡ ሲሆን እነዚህ የፀጉር ፎሊክሎች ልክ እንደ መጀመሪያው የቅንድብ ፀጉር 0.7-0.8 ሚሜ ዲያሜትር አላቸው.
የቅንድብ ንቅለ-ተከላ ከመደረጉ በፊት ለንቅለ-ተከላው የሚውሉ የፀጉር ፎሊክሎች(ስሮች) ከየትኛው የጭንቅላት ክፍል እንደሚሰበሰቡ ይወሰናል። ለዚህ በጣም ጠቃሚ የሆኑት የፀጉር ፎሊክሎች በጭንቅላት ጀርባ አንገት ላይ ያሉ ናቸው። ከዚህ አካባቢ በተጨማሪ በብብት እና በእጆች ላይ ያሉ የፀጉር ፎሊክሎችም እንደ ሁኔታው ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ። ምክንያቱም በጀርባ ጭንቅላት ላይ ወይም በብብት እና በክንድ ላይ ያሉት ፎሊኪሎች በሰውነት መዋቅር ምክንያት ጠንካራ ናቸው።
ጤናማ መልክ ያለው ቅንድብ እንዲኖር ለማስቻል በአማካይ 500 ስሮች(ፎለኪሎች)ችሊያስፈልግ ይችላል። አሁን ባለው የቅንድብ መጠን እና ውፍረት ላይ በመመስረት የሚተከሉት የጸጉር ፎለኪሎች ቁጥር እንደየሰው ሊለያይ ይችላል። እያንዳንዱ የቅንድብ ፀጉር ከሌሎቹ ፀጉሮች ጋር በተመሳሳይ አቅጣጫ ማደግ አለበት። ስለዚህም እኩል እና ተፈጥሯዊ መልክ እንዲኖራቸው የቅንድብ ፀጉርን ጥቅጥቅ ብሎ መትከል አስፈላጊ ነው.
ከቀዶ ጥገናው በኋላ በሽተኛው በሆስፒታል ውስጥ እንዲቆይ አይገደድም። ራስዎን አጋዠ ሳያስፈልግዎ ወደ ቤትዎ በማሽከርከር መመለስ የሚችሉ ሲሆን በአንድ ወይም በሁለት ቀናት ውስጥ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴዎ መመለስ ይችላሉ። ቅንድቡ ከተተከለ በኋላ አንዳንድ ፀጉሮች መርገፍ ይጀምራሉ ፣ ይህም ምንም የማያሰጋና መደበኛ ሲሆን ከአዳዲስ ፀጉሮች ጋር ፣ ቅንድቡ በጊዜ ሂደት ተፈጥሯዊውን መልኩን ንይዛል። ከንቅለ-ተከላ በኃላ የቅንድብ እና የዐይን ሽፋሽፍት እንክብካቤ አስፈላጊ ነው.
በኢንፌክሽን, በቆዳ ችግር, በሆርሞን ለውጦች ወይም ከመጠን በላይ ከሆነ የሰውነት መከላከል አቅም (immune system) ሊመጣ ይችላል:: የተመጣጠነ ምግብ እጥረት፣ የአካል ጉዳት፣ ወይም ስሜታዊ ውጥረቶች ቅንድብ እንዲቀንስ ሊያደርግ ይችላል። የታይሮይድ እጢ አስፈላጊውን ሆርሞኖችን ስለማይፈጥርም ሊሆን ይችላል። ካንሰርን ለመዋጋት የሚደረገው ኪሞቴራፒ በፍጥነት የሚከፋፈሉ ህዋሶችን ሁሉ የማጥፋት ጸባይ አለው፤ ይህም የፀጉር ፎሊክሎችን ያጠቃልላል ለዚህም ነው ሰዎች ይህንን ሕክምና በሚወስዱበት ጊዜ ፀጉር መርገፍ የሚያጋጥማችው።
በትክክል ከተሰራ እና መመሪያዎቹን ከተከተሉ, በአንድ ወር ውስጥ ተፈጥሯዊ የሚመስሉ ቅንድቦች ይኖሩዎታል እና የቅንድብ ንቅለ-ተከላ እንደነበረ ማንም አይረዳም.
የዓመታት ልምድ
ጤና ጣቢያዎች
ዶክተሮች እና ሰራተኞች
አገልግሎት የሚሰጡ ሀገራት
Copyright © 2022 Sultan Hair. All Rights Reserved.