ሱልጣን ሄር - የፀጉር ንቅለ-ተከላ - የአይቮሪ ኮስት የፀጉር ሽግግር

የጺም እና የቀድሞ ቀመስ ንቅለ-ተከላ

image

በFUE ዘዴ የጢም እና የቀድሞ ቀመስ ንቅለ-ተከላ ደረጃዎች

የፀጉር ሥር ለጋሽ ቦታ መወሰን፡- የተመረጠው ቦታ በቂ እና ጤናማ የፀጉር ሥር (follicles) ሊኖረው ይገባል። የጸጉሮው ክፍል የሚሰበሰብበትና የሚተከልበት ቦታ ከታወቀ በኋላ የለጋሹ ቦታ በጥቃቅን መርፌዎች ወይም በልዩ እስክሪብቶች ማደንዘዣ ይደረግለታል። የተሰበሰቡት የፀጉር ፎሊክሎች ተቆጥረው በልዩ ውህድ ተቀምጥው ለንቅለ-ተከላ ዝግጁ አንዲሆኑ ይደረጋል. ለ 100% ተፈጥሯዊ ገጽታ የፀጉር እድገት ማዕዘን ትክክለኛውን አንግል እና አቅጣጫ ግምት ውስጥ በማስገባት በተወሰንው ቦታ ላይ የፀጉር ፎሊክሎች በጣም በጥንቃቄ ይቀመጣሉ.

የጢም እና የቀድሞ ቀመስ ንቅለ-ተከላ አስደናቂ ውጤቶች፡- ጢም እና ቀድሞ ቀመስ በFUE ዘዴ ከተተከሉ በኋላ በታካሚው ፊት ላይ ምንም አይነት ጠባሳ ወይም የአካል ጉድለት ባያስከትልም በቀዶ ጥገናው ወቅት ትንሽ ህመም ይኖረዋል። ቀዶ ጥገናው ተጥናቆ ፀጉሩ በቋሚነት ከተተከለ እና መጠኑ ከተሰጠ በኋላ ልዩነቱን ወዲያውኑ ማየት ይችላሉ።

ከጢም ንቅለ-ተከላ በፊት

ጢም ንቅለ-ተከላ ከ 20-22 አመት ጀምሮ ሊተገበር ይችላል, ይህ የእድሜ ደረጃ ሆርሞኖች በ basal ደረጃ ውስጥ የሚሰበሰቡበትት ጊዚ ነው። የጎን ንቅለ-ተከላ እና የቅንድብ ንቅለ-ተከላ ከዚህ ንቅለ-ተከላ ጋር ተመሳሳይነት ያልው ሲሆን መደበኛ የሆነ ጸጉር የሊላችው ሰዎች የሚጠቀሙበት ዘዴ ነው። የጢም ንቅለ-ተከላ ከፀጉር ንቅለ-ተከላ የተለየ ነው፤ ምክንያቱም ሁሉም ሰው የተለያየ ጢም አለው፤ ይጢም መርገፍ ካለ በአካባቢው ያለው የጢም ድግግሞሽ የታቀደ እና ከአካባቢው ፀጉሮች ጋር የተጣጣመ ነው። ሕመምተኛው ሙሉ በሙሉ ጢም የሌለው ከሆነ በሚፈለገው ብዛት መሰረት ከ 1500 እስከ 300 የፀጉር ሥሮች ይለወጣል.

ከጢም ንቅለ-ተከላ በኃላ

ከጢም ንቅለ-ተከላ በኃላ የተደረግበት ቦታ በደም መርጋት ምክንያት ትንሽ ቀይ ይሆናል። ከ 24 ወይም 48 ሰአታት በኋላ የረጋው ደም ስለሚጸዳ የተተከለው ጢም በደመብ መታይት ይጀምራል። የጢም ሥሮችን ደጋፊ በሆኑ አካላት አካባቢ ቀይ ሆነው ሊታዩ ቢቸሉም በ1-2 ሳምንታት ውስጥ ይጠፋል። ከፀጉር አሠራር ጋር ተመሳሳይነት ያለው ይህ ዘዴ ዋጋው ግን የተለየ ነው። ይህ የሆነበት ምክንያት የጢም ሥሮች ንቅለ-ተከላ ከፀጉር ሥሮች ንቅለ-ተከላ የበለጠ ከባድ ስለሆነ ነው.

የቀድሞ ቀመስ ንቅለ-ተከላ ምንድነው?

ከከንፈሮች በላይ ፀጉር የሌላቸው ወይም ማወፈር የሚፈልጉ ሰዎች የፀጉር ንቅለ-ተከላ ሊደረግላቸው ይችላል ይህ የቀድሞ ቀመስ ንቅለ-ተከላ ይባላል። ይህ ክዋኔ በ FUE ንቅለ-ተከላ ዘዴ ይከናወናል። በዚህ ዘዴ, የአካባቢ ማደንዘዣ በማድረግ እና ከ2-3 ሰአታት የሚወስድ የማይክሮ ቀዶ ጥገና ይደረጋል።

ንቅለ-ተከላ ማድረግ የሚፈልጉ ሰዎች ከየትኛው የጭንቅላት ክፍል ላይ የፀጉር ሥሮቹ እንደሚወሰዱ ውሳኔ ይሰጣሉ። ከታካሚው የሚወሰዱት የፀጉር ፎሊክሎች፤ በ 0.7 ሚሜ አተኩሮ በሚተክሉ መሳሪያዎች ወደ ተፈለገው ቦታ ይተክላሉ።

ከመጀመሪያው ንቅለ-ተከላ በኋላ በግምት 4 ወራት ያህል, የሳሱ ቦታዎች ካሉ, አዲስ የመትከል ሂደት ሊደረግ ይችላል። ይህ ንቅለ-ተከላ በጣም አስቸጋሪና ከፍተኛ ጥንቃቂ ስለሚያስፈልገው, መከናወን ያለበት ልምድ ባካበቱ ባለሙያዎች ብቻ ነው። አለበለዚያ ንቅለ-ተከላው አሉታዊ ውጤቶችን ሊሰጥ ይችላል.

ከቀድሞ ቀመስ ንቅለ-ተከላ በፊት ሂደቱ እንዴት ይመስላል?

ከስፔሻሊስት ሐኪምዎ ጋር በሚደረገው ስብሰባ, ለእርስዎ ተስማሚ ስለሆነው የጢም ተከላ እቅድ ይወሰናል። በዚህ የእቅድ ሂደት ውስጥ ምን ያህል የፀጉር ሥሮች እንደሚተከሉ፤ ወደ የትኞቹ ቦታዎች እና በየትኛው ዘዴ እንደሚተገበሩ ይወሰናል። የተተከሉት ፀጉሮች በሰውነትዎ ጤናማ እና ምቹ በሆነ መንገድ እንዲታገዙ የፀጉር ንቅለ-ተከላ ከሚያስፈልገው በላይ መደረግ የለበትም። ስለዚህ, የልዩ ባለሙያ ሐኪምዎን ምክሮች በደምብ ግምት ውስጥ ማስገባት የተሻለ ነው።

እርስዎ ትኩረት የሚሰጡበት ሌላው ጉዳይ የቀድሞ ቀመስ ተከላ ዘዴ ነው። ያለምንም ጠባሳ እና በትንሽ ጉዳት የሚተገበር የሆነው በቅርብ ዓመታት ውስጥ በሰፊው እየተሰራበት ያለው የFUE ቴክኒክ ለዚህ ትመራጭ ነው።

የቀድሞ ቀመስ ንቅለ-ተከላ በሚደረግበት ቀን ግምት ውስጥ መግባት ያለባቸው ነጥቦች

ፊትዎን ላለመንካት በቀዶ ጥገናው ቀን በቀላሉ የሚለብሱ እና የሚወለቁ ልብሶችን ይምረጡ። ሲጋራ ማጨስ ቀዶ ጥገናውን እና የፈውስ ሂደቱን አስቸጋሪ ስለሚያደርግ ከንቅለ-ተከላ በፊት ማጨስ የለብዎትም። የተጋነኑ ጥያቄዎችን ሳያቀርቡ ምክንያታዊ ይሁኑ። ቀላል ምግብ መብላት አለቦት እና የጥጋብ ሲሰማዎት ወደ ሆስፒታል ይሂዱ። መድሃኒቶችን በመደበኛነት የሚጠቀሙ ከሆነ ከቀዶ ጥገናው በፊት ሁል ጊዜ ለሐኪምዎ ማሳወቅ አለብዎት ። ዶክተርዎን ሳያማክሩ መድሃኒት አይጠቀሙ፡፡ አልኮል አይጠጡ. ፂም(ቀድሞ ቀመስ) ካለቦት መላጨት አለበት። በቀዶ ጥገናው ቀን በሆስፒታሉ ውስጥ ትንታኔ ከተደረገ በኋላ አስፈላጊ ከሆነ ይላጩ። ካፌይን ያላቸውን መጠጦች አይጠጡ።

የቀድሞ ቀመስ ንቅለ-ተከላ ሂደት, ደረጃ በደረጃ

ከፀጉር ንቅለ-ተከላ ጋር የሚመሳሰል ቀዶ ጥገና በፊትዎ ላይ ስለሚደረግ የበለጠ ጥንቃቄ የተሞላበት ቀዶ ጥገና ነው። ምክንያቱም ፊትዎ ለጠባሳዎች እና ላልተጠበቁ ጉዳቶች ተጋላጭ ስለሆነ ይህን ለመከላከል የበለጠ ጥንቃቄና የበለጠ ትኩረት ያስፈልገዋል። ህመምን ለመከላከል ከቀዶ ጥገናው በፊት የላይኛው የከንፈር አካባቢ ማደንዘዣ ይደረጋል። የአንገት ናፕ ተመራጭ ለጋሽ አካባቢ ቢሆንም ነገር ግን እንደ ሁኔታው ክንድ እና እግር ለጋሽ ቦታ ሆነው ሊመረጡ ይችላሉ። የፀጉር ፎሊክሎች በ FUE ዘዴ እና በማይክሮሞተር እርዳታ አንድ በአንድ ይሰበሰባሉ። በቀዶ ጥገናው አካባቢ የፀጉር ቆጠራ መሰረት ከ300 እስከ 500 የሚጠጉ የፀጉር ፎሊክሎች ይሰበሰባሉ። እነዚህ ፎሊሌሎች ተሰብስበውና ተስተካክለው በፂም አካባቢዎ ላይ ወደተዘጋጁ ቻናሎች ይተከላሉ። የተተከለው ቦታ ክፍት ሆኖ ለ 3 ቀናት በለጋሽ ቦታ ላይ ማሰሪያ ተደርጎ ይቆያል። በዚህ ጊዜ ውስጥ የተተከለውን ቦታ አይታጠቡ። የማገገሚያ ጊዜ ከቀዶ ጥገናው ከ 10 ቀናት በኋላ ነው። በዚህ ሂደት ውስጥ በሦስተኛው ቀን ከመጀመሪያው ትጥበት በኋላ የደረቁ ተፈርፋሪ የጸጉር ቁስሎች በመርገፍ የፀጉር ሥሮች ማገገም ይጀምራሉ። ሰውዬው ቀድሞ ቀመስ የሌለው ከሆነ አንድ ቀዶ ጥገና በቂ ላይሆን ይችላል። በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ, ሁለተኛው ቀዶ ጥገና የሚከናወነው በግምት ከ 8-9 ወራት ውስጥ የተተከሉ ሥሮች ወደ ቦታቸው ከተስተካከሉ በኋላ ነው። ቀድሞ ቀመስ ከተተከለ በኋላ የሚበቅሉት ፀጉሮች ከ15 ቀናት በኋላ በመቀስ ሊቀነሱ ሱችላሉ። ምንም እንኳን በሁሉም ሰው ላይ ባይታይም ከቀዶ ጥገናው ከ2-3 ሳምንታት በኋላ ድንገተኛ መርገፍ ሊታይ ይችላል። በአራተኛው ወር አጋማሽ ላይ ድንገተኛ መርገፉ ከቆመ በኋላ ፀጉሮች እንደገና በመደበኛነት ማደግ ይጀምራሉ። ከ 6 ወር በኋላ የቀድሞ ቀመስ የፀጉር ስሮች ቦታቸውን መያዝ ይጀምራሉ። በመጨረሻም በመደበኛነት ማደግ ይቀጥላሉ።

20+

የዓመታት ልምድ

4

ጤና ጣቢያዎች

40+

ዶክተሮች እና ሰራተኞች

60+

አገልግሎት የሚሰጡ ሀገራት

ስልክ ቁጥርዎን ይተዉት።

እንጠራሃለን።

Sultan Hair

በፊት እና በኋላ

የቀዶ ጥገናውን በፊት እና በኋላ ያሉትን ፎቶዎች አሁን ይመልከቱ።



Sultan Hair

ቪዲዮዎች

Türkçe
Türkçe
Türkçe
Türkçe
Türkçe
Türkçe
Türkçe
Türkçe
ይደውሉልን
WhatsApp